የትከሻ መድረቅ (Frozen Shoulder) # Eye info doctor

world journals
0

 የትከሻ መድረቅ (Frozen Shoulder) 


ፍሮዝን ሾልደር (የትከሻ መድረቅ ) በትከሻ አካባቢ ከሚታዩ ችግሮች አንዱ ሲሆን በትከሻ ላይ ህመም እና መድረቅን ያስከትላል፡፡ 


ፍሮዝን ሾልደር በማን ላይ ይታያል? 


- እድሜያቸው ከ40 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች

- በሴቶች በተለይ ይታያል

- በተለያዩ ምክንያቶች ትከሻ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይንቀሳቀስ ሲቀር (ለምሳሌ በትከሻ ጉዳት/ ቀዶ ህክምና) 

- ተጓዳኝ በሽታ ያላቸው (ለምሳሌ ስኳር ፣ ታይሮይድ) 


ምልክቱ 


ሶስት ደረጃዎች ሲኖሩት የመጀመሪያው ትከሻ ሲንቀሳቀስ ህመም መሰማት ሲሆን ሁለተኛው ትከሻ መድረቅ ወይም ማንቀሳቀስ መቸገር ነው፡፡ በሶስተኛው ደረጃ ላይ በህመም እና ትከሻ ድርቀት ላይ ማገገም ይታያል፡፡ 


ህክምናው 


- ፊዚዮቴራፒ

- በትከሻ የሚሰጥ መርፌ 


ተመሳሳይ ችግር ካለዎት በአጥንት ስፔሻሊስት ሀኪማችን ጋር ቀርበው ይታዩ።

Post a Comment

0Comments

Post a Comment (0)