የተረከዝ ህመም (Heel Pain) #Eye info doctor

world journals
0

 የተረከዝ ህመም (Heel Pain) 



ከቁርጭምጭሚት በታች ከሚገኙ አጥንቶች ትልቁ ነዉ፡፡የተረከዝ ህመም ሲያጋጥም ሰዎች ብዙ ጊዜ ችላ ሲሉት የሚታይ ቢሆንም እየቆየ ሲሄድ ከመካከለኛ እስከ ከፍተኛ ችግርን ያስከትላል፡፡ 


ችግሩን የሚያመጡ መንስኤዎች

• በእድሜ መግፋት

• ምቾት የሌለዉ ጫማ መጠቀም

• ረጅም ሰአት መቆም እና ረጅም የእግር መንገድ

• እግር ላይ የደረሰ አደጋ (ስብራት)

• የእግር ጅማት ህመም

• የእግር መገጣጠሚያዎች ላይ ዉሃ አዘል እባጭ 

• የአጥንት መሳሳት

• የስኳር ህመም እና ከፍተኛ የደም ግፊት መጠን ናቸው። 


መች ወደ ህክምና መሄድ አለብን? 


• ህመሙ የተባባሰ ከሆነ

• በድንገት የመጣ ህመም

• የተረከዝ መቅላት ወይም እብጠት

• መራመድ ካልተቻለ 


የተረከዝ ህመም እንዳይከሰት የሚረዱ መከላከያ መንገዶች 


• የሚመቹ ጫማዎችን መጠቀም

• እንቅስቃሴ ከመደረጉ በፊት ጡንቻን ማሳሳብ

• የተመጣጠነ ምግብ መመገብ

• የተመጣጠነ የሰዉነት ክብደት 

• ረጅም ሰአት ከመቆም እና ረጅም የእግር ጉዞ ከማደረግ መቆጠብ ናቸው። 


የተረከዝ ህመም ህክምና 


• በቂ እረፍት ማገኘት

• የህመም ማስታገሻ መድሐኒቶች መጠቀም

• በቀን ሁለት ጊዜ በበረዶ ከ10-15 ደቂቃ ማሸት

• በመርፌ የሚሰጥ ህክምና

• የፊዚዬቴራፒ ህክምና

Post a Comment

0Comments

Post a Comment (0)