#የእርስዎ_ልጅ_ብትሆን_ምን_ያደረጉ_ነበር ❓️😭😭
ታሪኩ እንዲህ ነው 👇
ገና የ2 አመት ልጅ ናት። ቤተሰቧ እግሮቿ ቀጥ ያሉ እንዳልሆኑ እና ጠማማ እንደሆኑ አስተዋሉ። ስጋታቸውንም ለአካባቢው ባህላዊ አጥንት ጠጋኝ/ወጌሻ ነገሩት። ወጌሻም የህፃኗ አጥንት ትክክለኛ ቦታው ላይ እንዳልሆነና መስተካከል እንዳለበት ይነግራቸዋል።
ከዚያም ደህና የነበረውን የ2 አመት ልጅ እግር ያለ ምንም ማደንዘዣ መድሃኒት በእንጨት ቀጥቅጦ በቀርከሃ ቀጥ አድርጎ በጥብቅ አሰረው።
ያለምንም ማደንዘዣ ህመሙን አስቡት 😭😭😭
ቤተሰቧችንም ምንም ይሁን ምን እንዳይፊታ ነገራቸውና ወደ ቤት ላካቸው።
ልጂቷ ከዚያ በኋላ እያለከሰች ነበር ግን ቤተሰቦቿ ችላ አሏት! ከጥቂት ቀናት በኋላ እግሯ ከእግር ጣት ጀምሮ መጥቆር ጀመረ እና በ3ኛው ቀን ሆስፒታል ስትደርስ እግሯ ጋንግሪን ሁኖ በስብሶ ነበር 😥.
ህፃኗ ላይ የነበረው እና ወላጆችን ያሳሰበው የአጥንት ጉዳይ እሰከ 2 አመት ሊከሰት የሚችልና ከዚያ በኋላ በራሱ ጊዜ የሚስተካከል የአጥንት እድገት ሂደት ነበረ !
በተፈጠረው ክስተት በጣም አዘንን😥 በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለብን ተወያይን:: ከዚያም ህፃኗን ለማየትና ቤተሰቧን ለመምከር አራት ስፔሻሊስት ሐኪሞች ጋር ሁነን ወደ ተኛችበት ክፍል አመራን። ግን እዚያ አልነበሩም (ጠፍተዋል)።
በጠዋት ከሆስፒታሉ ወጥተው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሊወስዷት እንደሄዱ በአቅራቢያው ያለ አንድ ታካሚ ነገረን። 'እግዚአብሔር ይርዳት እና ድና በሁለት እግሮቿ ስትራመድ ማየት በጣም ያስደስተናል' ይህን ብቻ ነበር በጊዜው ያልነው ።
ከአንድ ሳምንት በኋላ ሴት አያቷ ህፃኗን ይዘው ወደ ሌላ ክሊኒክ መጡ። ችግሯ ከጉልበቷ በላይ እየገፋ ከጉልበቷ እና ከጭኗ በሚወጣ ኢንፌክሽን ባለው ፈሳሽ ተበክላለች። የልጅቷን የአጎት ልጅ ጨምረን ስለጉዳዩ ከ አንድ ሰዓት ያላነሰ ቁጭ ብለን ተወያየን።
ሕፃኗን ለቀዶ ጥገና ሕክምና ወደ ሆስፒታል እንዲመልሷት አጥብቀን ነገርናቸው። አያቷ ተስማምተው ከክሊኒኩ ወጡ። ነገር ግን ልጅቷን ቀኑን ሙሉ ወደ ሆስፒታል አላመጡም።
ሰለቀሩብኝ ለመጠየቅ ስልክ ቁጥሩን ከካርድ ፈልጌ ደወልኩ እና የልጅቷ አክስት ስልክ ቁጥር ነው። ወደ ሆስፒታል አልመጡም ምን ሁነው ይሆን ስላት 'ለመወሰን ወላጆቿ ስላልነበሩ ወደ ቤት እንደመለሷት' ነገረችኝ። እሺ እባካችሁ ተጨማሪ ስሕተቶችን አትሥሩ፣ ሂዱና ለወላጆች ንገሯቸው እና ሕፃኗን ጠዋት ወደ ሆስፒታል አምጧት አልኩ።
አሁን ከተነጋገርን 72 ሰዓታት አልፈዋል። ስልካቸው አይሰራም። ምናልባት ያቺ ህፃን እስካሁን ምንም አይነት ህክምና አላገኘችም😥😥.
ልጅዎ ብትሆን ምን ያደርጋሉ ?
👉 አብዛኛዎቻችን ወጌሻ ቁስል የሌላቸው ወይም የተዘጉ ስብራቶችን ወይም ውልቃቶችን ያክማል ብለን እናስባለን።
አሁን አሁን ግን ክፍት ወይም ቁስል ያላቸውን ሰብራቶች ሁሉ ንፁህ ባልሆነ ጨርቅ ጠቅልለው ጥብቅ ባለ ቀርከሃ አስረው ለተወሰነ ቀናት ካቆዩ በዋላ እና በኢንፌክሽን ከተያዙ በኋላ ወደ ሆስፒታል እየላኩ ነው። ሌላው ትኩረት ፈላጊ ጉዳይ ደግሞ ወጌሾች ዝንፍ/ጠመም ያለ የአካል ክፍል ሁሉ ለማስተካከል እየሞከሩ ነው😲😳።
🔊 ይህንን ባህላዊ እና ጎጂ አሰራር ለመግታት ሥርዓት መኖር አለበት። ሁሉም የሚመለከተው ማህበረሰብ ሊሰራበት ይገባል። በዚህ ጉዳይ ላይ መንግስት ፖሊሲ ሊኖረው ይገባል:: በልጆች መብት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች በዚህ ላይ መስራት አለባቸው።
በሆስፒታል ውስጥ ሊታከም ለሚችል ቀላል ችግር እንደዚህ አይነት ከባድና ውስብስብ ችግር እንዳይፈጠር እንረባረብ!
#ሚዳከኝ
#የምእራብሸዋዞንጤናቢሮ
#ኦሮሚያጤናቢሮ
#ጤናሚኒስትር
#የሴቶች እና የህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
#የኦሮሚያሀኪሞችማህበር
#የኢትዮጵያህክምናማህበር
#የኢትዮጵያአጥንትቀዶጥገናማህበር #ESOT
✍️ በዶ/ር ሚልኬሳ ሁንዴ (የአጥንት ቀዶ ጥገና ሐኪም) እና
በዶ/ር ኤፍሬም በቀለ (የአጥንት ቀዶ ጥገና ሐኪም) የተፃፈ