@Eye info media # Ethiopian defens armey journal

world journals
0

 👉 የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ወታደሮች ለሶማሊያ ሠላም መስፈን የሚያደርጉት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው‼






በሶማሊያ ኪስማዩ የሚገኙት የአሜሪካ ወታደራዊ አመራሮች ከኢትዮጵያ 7ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ወዳጅ ቦጋለ ጋር በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል።

ኮሎኔል ወዳጅ ቦጋለ ሻለቃው ከአትሚስ የተሰጠውን ተልዕኮ መነሻ በማድረግ በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች አቅማቸውን እንዲያዳብር የተለያዩ የመሳሪያ ስልጠናዎችን መስጠታቸውን ተናግረዋል።

ሻለቃው በሚሸፍንበት የግዳጅ ቀጣና ሁሉ  በእግር እና በተሽከርካሪ በመታገዝ የቅኝት ተግባራትን  በማድረግ በአካባቢው የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከአሸባሪው የአልሸባብ ቡድን ስጋት ነፃ እንዲሆኑ ተደርጓል ብለዋል።

ኮሎኔል ወዳጅ በቀጣይ ከአትሚስ የሚሰጠንን ተልዕኮ መነሻ በማድረግ በአካባቢው ከሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች እና ከአሜሪካ ወታደሮች ጋር በመቀናጀት አልሸባብ ላይ የማያዳግም ርምጃ እንወስዳለን ሲሉ ተናግረዋል።

በኪስማዩ የሚገኙት የአሜሪካ ወታደሮች አስተባባሪ ሻምበል ሄረን ኤቨን በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሶማሊያ ሠላም ማስፈን የሚያደርጉት አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን በዶሎ አልሸባብ ላይ የወሰዳችሁት እርምጃ ጀግንነታችሁን እና አሸናፊነታችሁን  የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሠላም ወሳኝ የሆነች ሀገር መሆኗን እኛ የአሜሪካ ወታደሮች በምንፈፅመው የእለት ከእለት ግዳጅ ማረጋገጥ ችለናል ሲሉ ተናግረዋል።

በቀጣይ አልሸባብን ከመላው ሶማሊያ ለማጥፋት እና የተረጋጋች እንዲሁም ሠላም የሰፈነባት ሶማሊያን ለመገንባት የአሜሪካ ወታደሮች እና የኢትዮጵያ ወታደሮች በጋር የሚፈፅሙት ግዳጅ ወሳኝ ነው ብለዋል።

Via~FDRE Defense Force

Post a Comment

0Comments

Post a Comment (0)