" የባይደን አስተዳደር የወሰደው እርምጃ የአሜሪካ እና የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ዕርዳታ ወደ ኢትዮጵያ መላክን ለማስቀጠል መንገድ የሚከፍት ነው " - ፎሬይን ፖሊሲ ድረገፅ
አሜሪካ ፤ ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈችውን ፍረጃ ማንሳቷን " ፎሬይን ፖሊሲ " ዘግቧል።
የፕሬዜዳንት ባይደን አስተዳደር ፤ " ኢትዮጵያ አሁን ላይ በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ውስጥ እየተሳተፈች አይደለችም " በሚል ለኮንግረሱ ማሳወቁ ተነግሯል።
ይህ ውሳኔ የአሜሪካ እና የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ዕርዳታ ወደ #ኢትዮጵያ መላክን ለማስቀጠል መንገድ የሚከፍት ነው ተብሏል።
አሜሪካ ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራት ግንኙነት መሻከሩ ፤ በተለይ የኢኮኖሚ ማዕቀቦችን መጣሏ የሚዘነጋ አይደለም።
አሁን ላይ ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ የባይደን አስተዳደር የወሰደው እርምጃ ዋሽንግቶን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል እየሰራች ባለችበት ወቅት መሆኑን ፎሬይን ፖሊሲ በድረገፁ አስነብቧል።