No title

world journals
0

 



መንግስት ሕገ መንግስታዊ ስርአቱን በኃይል በመናድ ጠርጥሬአቸዋለሁ ብሎ በቁጥጥር ስር ያዋለቸው ቡድኖችና ግለሰቦች በሕገ ወጥ በመሳሪያ ግዥና ሽያጭ ላይ መሰማራታቸውን የሚያሳይ አፈትልኮ የወጣው የድምጽ መረጃ አጋለጠ፡፡


አፈትልኮ የወጣው የጽምጽ መረጃ ቅጂ እንደሚያሳየው ሕገ መንግስታዊ ስርአቱን በኃይል ለመናድ በአዲስ አበባ በተለይም በተለምዶ ወሰን ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የመሳሪያ፣የተተኳሽ እና ሕገ ወጥ ወታደራዊ ዩኒፎርሞች ግዥና ሽያጭ እየተካሄደ እንደሆነ ያጋልጣል፡፡

በድምጽ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው ዳዊት የተባለ ግለሰብ ሞላልኝ እና አዲስ ከተማሉ ሌሎች ግለሰቦች ጋር የሚያደርጉት የስልክ መረጃ ልውውጥ በሕገ ወጥ የመሳሪያ ግዥ፣ተተኳሽ እና የደንብ ልብስ በማሰፋት ወደ ተለያዩ አከባቢዎች እንደሚያሰራጩ ያስረዳል፡፡
በስልክ ልውውጡን ተተኳሾችን ባለ ስድስት እና ባለ ስምንት አንዱን በ140 ብር እንዲሁም ትልቁ ዕቃ እያሉ የሚጠሩትን የመሳሪያ አይነት ደግሞ እስከ 120 ሺህ ብር እንደሚገዙና እንደሚሸጡ በመረጃው ተገኝቷል፡፡

በድምጽ መረጃው መሰረት መለዮዎችን በብዛት ለማንቀሳቀስ ችግር እንዳያጋጥም አስር አስር ብቻ እየተረከቡ መውሰድ ተገቢ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ መንግስት ሰላምና ሕግ የማስከበር ኃላፊነቱን እየተወጣ ሲሆን ማሕብረተሰቡ በአዲስ አበባ የተለያዩ አከባቢዎች መሰል እንቅስቃሴዎች ሲመለከት በተለይም ሰዋራ ቦታዎች የሚፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶችን በመከታለ ጥቆማ ለፖሊስ በመስጠት የከተማዋን ደህንነት ሊጠብቅ ይገባል፡፡

Post a Comment

0Comments

Post a Comment (0)