የጉልበት ህመም(knee joint pain)
![]() |
የጉልበት ህመም(knee joint pain)
የጉልበት ህመም በማኝኛውም ማህበረሰብ የሚከሰት ቢሆንም እድሜያቸው በገፋና ከፍተኛ የሰውነት ክብደት ባላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ጎልቶ ይታያል፡፡
የጉልበት ህመም ምክንያቶች ምንድናቸው?
• የጉልበት ላይ ቀጥተኛ ጉዳት ሲኖር
• የጉልበት አንጓ ብግነት
• የጉልበት መገጣጠሚያ ውስጥ መበላት
• በጉልበት አካባቢ የሚፈጠር ኢንፌክሽን
• በጉልበት አካባቢ ወይም በሎሚ ላይ በስብራት ወይም በውልቃት የሚመጣ ህመም
• የጉልበት አካባቢ ያሉ ጅማቶች መጎዳት ወይም ጫና መፈጠር
• የጉልበት አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች መጎዳት ወይም መኮማተር
• የጉልበት ጀርባው አካባቢ ላይ በሚፈጠር እብጠት
• በዩሪክ አሲድ መብዛት አማካይነት የሚከሰት ህመም ወይም ሪህ
• በከፍተኛ ደረጃ የሰውነት ክብደት መጨመር
• ምቾት የሌላቸውን ጫማዎች አዘውትሮ መጠቀም
• የጉልበት አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች መስነፍ
የጉልበት ህመም እንዴት እንከላከል?
• ተመጣጣኝ ክብደት ይኑርዎት
• ምቾት የሚሰጡና ተረከዝ ያልበዛባቸው ጫማዎችን ያዘውትሩ
• ተከታታይነት ያለው አካላዊ እንቅስቃሴ መስራት
በጉልበት አካባቢ የሚፈጠር ኢንፌክሽን በቶሎ ካልታከመ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ጉልበት ላይ ያስከትላል። ስለዚህም የጉልበት አካባቢ ላይ እብጠት መቅላት እና ትኩሳት ሲኖር በአስቸኳይ የአጥንት ስፔሻሊስት ሀኪም ጋር ቀርበው መታየት አለብን ።
የጉልበት ህመምና ሌሎች የመገጣጠሚያ ህመሞች የሚያስቸግርዎት ከሆነ የአጥንት ስፔሻሊስት ሀኪሞቻችንን ይጎብኙን።


